Rules And REGULATIONS

The Center of Safety, Discipline, and Innovation!
የደህንነት፣ የስርዓት እና የፈጠራ ማዕከል!!


Students should follow these Rules

  1. መግቢያ

     

    በሀገራችን በየደረጃው የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት ት/ቤቶች የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ትምህርት የዕድገት ሁሉ ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ ለሁለንተናዊ ልማት መፋጠን ትልቁን ድርሻ ይይዛል፣ ትምህርት ተመራማሪና ችግር ፈቺ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችልና የህብረተሰቡን አመለካከት ወደ እድገት አቅጣጫ የሚመራ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ሳይንሳዊ ግኝቶች ጋር በማስተዋወቅ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ባህላዊ ዕድገቶችን የሚያፋጥን መሣሪያ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ት/ቤቶቻችን በሰከነና ቀልጣፋ አመራር የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማከናወን ይቻል ዘንድ የተማሪውን ስነምግባር በተፈለገው አቅጣጫ ለማነፅ መብቱንና ግዴታዎቹን ማሳወቅ አስፈላጊ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ተቋማት አንድ ወጥ የአመራርና የርምጃ አወሳሰድ አፈፃፀም መኖሩ ተገቢ በመሆኑ ይህ የተሻሻለ የመጀመሪያ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የተማሪዎች መተዳደሪያ መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ተዘጋጅቷል፡፡

     

     

     

     

     

    አንቀፅ 1፡ የተማሪዎች መብት

    1.1. የመማር፣ ጠይቆ የመረዳትና የማወቅ ፣

    1.2. በት/ቤቱ የትምህርት ግብዓቶች የመጠቀም ወይም አገልግሎት የማግኘት፣

    1.3. የትምህርታቸውን ውጤትና የምስክር ወረቀት በወቅቱ የማግኘት፣

    1.4. የት/ቤቱን የክፍል ውስጥ መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች መመሪያዎችን የማወቅና የማግኘት፣

    1.5. ከመምህራን ጋር ተገቢ የሆነ የመማር ማስተማር ግንኙነት በመፍጠር ድጋፍና እርዳታ የማግኘት፣

    1.6. የሚደርስባቸውን በደልና ቅሬታ በየደረጃው ላሉ የት/ቤቱ አካላት የማቅረብ፣

    1.7. ስለመምህራን የማስተማር ክህሎት የመገምገም አስተያየት ሲጠየቁ የመስጠት፣

    1.8. ከመማሪያ ክፍል ውጭ የሚከናወኑ የተጓዳኝ ትምህርት ኘሮግራሞች ላይ የመሳተፍ፣

    1.9. በትምህርት ቤት አደረጃጀቶች ውስጥ ለተማሪዎች ከሚሰጠው ልዩ ልዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የመምረጥና መመረጥ፣

    1.10. ከት/ቤት ወይም በቅርብ ከሚገኝ የጤና ማዕከል የመጀመሪያ ዕርዳታ የማግኘት፣

    1.11. በት/ቤት የዕቅድ ዝግጅትና የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ በተወካዮቻቸው አማካኝነት መሳተፍ፣

    1.12. ተወካዮቻቸውን በየደረጃው ላሉ የኃላፊነት ቦታዎች የመምረጥ፣

    1.13 ትምህርት ቤቱ በማያዘጋጀው የመጠናከሪያ ትምህርት መሳተፍ

     

    አንቀፅ 2፡ የተማሪዎች ግዴታ

    2.1.  በት/ቤት በሚወጣው የትምህርት ኘሮግራም መሠረት የመገኘት፣

    2.2 ያለበቂ ምክንያት ከት/ቤት አለመቅረት፣

    2.3.  በት/ቤቱ ውስጥና በዙሪያው ተማሪዎች በህይወታቸው ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ተብሎ ከተከለከሉ ሥፍራዎች እራስን ማራቅ፣

    2.4.   በክፍል ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት በግልም ሆነ በቡድን በጥሞና የመከታተል፣

    2.5.  የክፍል ሥራ፤ የቤት ሥራ፤ የቡድን ሥራ የሚሰጡ የችሎታ መመዘኛዎችን ሠርቶ አጠናቆ በጊዜው የማቅረብ፣

    2.6.  የት/ቤቱ ኃላፊዎችና መምህራን በአግባቡ የሚሰጡትን ድጋፍ ምክርና መመሪያ መፈፀም፣

    2.7. ሴት ተማሪዎችን ከመተንኮስ፣ ከማስፈራራት ከመድፈር ከመደባደብና ሰብአዊ መብታቸውን ከመጋፋት መቆጠብ፣

    2.8. ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመግባባት መስራትና መማር፣

    2.9. ከማንኛውም የቡድን ጠብ አምባጓሮና ጉልበተኝነት ተግባር ራስን ማቀብ፣

    2.10. ለመምህራን፣ ለሠራተኞች፣ ለትምህርት አመራሮችና ለጓደኞቻቸው ተገቢውን ክብር መስጠት፣ /አለመዝለፍ፣ አለማንጓጠጥ፣ አለመስደብ፣ አለመዛት፣ አለማንቋሸሽ……ወዘተ/

    2.11. የመማሪያ መጽሐፍትን ሌሎች የትምህርት መሣሪያዎችን በጥንቃቄ መያዝና መጠቀም አለማበላሸት፣

    2.12. የትምህርት ጊዜን በማይሻማ ሁኔታ ዕውቀቱንና ጉልበቱን ለትምህርት ቤቱና ለአካባቢው ህብረተሰብ አገልግሎት የማዋል፣

    2.13. ለጋራ ጥቅም ደህንነተና ለልማት መስራት፣

    2.14. የት/ቤቱን ንብረት የመጠበቅ / መቀመጫ ወንበሮችን፣ የመማሪያ ክፍሎችን፣ መስኮቶችን፣ ምድረ ግቢውን በንፅህና መያዝና መንከባከብ/

    2.15. በት/ቤቱ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም በአካልና በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሣሪያ ይዞ አለመገኘት፣

    2.16. በት/ቤት ግቢ ውስጥ ማንኛውንም አይነት የሀይማኖትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች አለማካሄድ፣

    2.17. ሕጋዊ ያልሆኑ ስብሰባዎች ላይ ያለመሳተፍ፣

    2.18. የግልና የጋራ ንፅህናን መጠበቅ፣

    2.19. በደንቡ አንቀፅ 17 መሰረት የተፈቀደውን ሥነ-ሥርዓት የተከተለ የደንብ ልብስ አለባበስና የፀጉር አያያዝ መጠቀም፣

    2.20. የት/ቤቱን የደንብ ልብስ አዘውትሮ መልበስ፣

    2.21. በትምህርት ሰዓት ያለ በቂ ምክንያት በት/ቤት ቅጥር ግቢ አለመዟዟር፣

    2.22. የት/ቤቱን አጥር ዘሎ አለመውጣት /አለመግባት/ በአጥር አለመቀበልና አለማቀበል፣  መታወቂያ አሳይቶ መግባት እና መውጣት

    2.23. ለትምህርት ቤቱም ሆነ ለህብረተሰቡ ታማኝ መሆን፣

    2.24. አለማርፈድ እና ያለበቂ ምክንያት አለመቅረት፣

    2.25. ሲጋራ አለማጨስ መጠጥ ጠጥቶ አለመገኘት ጫትና ሌሎች አደንዛዥ ዕጾችን አለመጠቀም፣

    2.26. የስርቆት ወንጀል አለመፈፀም፣ ፈተና መኮረጅ ቁማር መጫወት ከመሳሰሉ ሕገወጥ ድርጊቶችና ከሌሎተ ጥፋቶች መራቅ፣

    2.27.  በት/ቤት ግቢ መታወቂያ ይዞ መገኘት ሲጠየቅ የማሳየት፣

    2.28.  ማንኛውንም ዓይነት ኤሌክትሮኒክስ (ላፕቶፕ፤ታፕና ሞባይል) መገልገያዎች በትምህርት ቤት ግቢ ይዞ መገኘት፤

    2.29  ትምህርት ቤቱ ከተማሪ መገናኛ መፅሀፍ የፊት ገፆች ላይ የሰፈሩ የተማሪ ማሰልጠኛ ማንዋል በትክክል አንብቦ ተግባራዊ ማድረግ

    2.30 የቤተ ክፍል ሃላፊ የሚፅፈውን አስተያየት ለወላጅ በማሳየት ለአስተያየቱ ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግ  እና ወላጅ አስፈርሞ መመለስ

    አንቀፅ 3፡ ግዴታቸውን በማይወጡ ተማሪዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች

    3.1. ተከታታይ የምክር አገልግሎት የሚያሰጡ ግድፈቶች /ጥፋቶች፣

    3.1.1. በተደጋጋሚ የማርፈድ፣

    3.1.2. በተደጋጋሚ ያለበቂ ምክንያት መቅረት፣

    3.1.3. በተማሪዎች መካከል የሚከሰቱ ቀላል የሀሣብ ግጭትና ያለመግባባት፣

    3.1.4. የክፍል ውስጥ ስነ-ስርዓትን ያለማክበር በክፍል መረበሽ መጮህ፣ ወዘተ፣

    3.1.5. በተደጋጋሚ ሁኔታ የቤት ሥራዎችን፣ የቡድን ሥራዎችን፣ የክፍል ሥራዎችን ያለመስራት ፣

    3.1.6. በክበባት ያለመሳተፍ፣

    3.1.7. የትምህርት መሣሪያ ይዞ አለመገኘት፣

    3.1.8. አጥር ዘሎ መግባትና መውጣት፣

    3.1.9. የት/ቤት ንብረትን በቸልተኝነት ማበላሸት፣

    3.1.10. በትምህርት ግቢ ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ይዞ መገኘት

    3.1.11.የተከለከሉ በዓላትንና ትምህርታዊ ጉብኝቶችን ለማካሄድ ሙከራ ማድረግ

    3.1.12. የተከለከሉ የደንብ ልብሶች፤የፀጉር አበጣጠርና መዋቢያዋችን የመጠቀም

    3.1.13 . በፋብሪካ  የተዘጋጁ ምግቦችን ወደ ትምህርት ቤት ይዞ መምጣት እና መጠቀም

    3.1.14   የወላጅን ፊርማ የግንኙኘ መፃፍ እንዲሁም ፈተና ወረቀት ላይ አስመስሎ መፈረም

     

                3.2. የምክር አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነትን በተመለከተ

         3.2.1. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 3.1 የተመለከቱትን ጥፋቶች በተደጋጋሚ ለሚፈፅሙ ተማሪዎች የቤተ ክፍል ሀላፊ የተማሪውን ሥነሥርዓት ለማስከበር ከተመረጡ ተማሪዎች ጋር በመሆን የተማሪውን በቀላል የጥፋተኝነት ደረጃ በየጊዜው የተመዘገቡትን ጥፋቶች እየተከታተሉ የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፣ ስለተሰጠው የምክር አገልግሎት መረጃ በተማሪው ማህደር ይቀመጣል፣

       3.2.2. የተማሪው/ዋ ጥፋት መረጋገጥ በተማሪው የመማር ሁኔታ ላይ ችግር ይፈጥራል ተብሎ ሲታመንበት ወላጅ በልጁ ጉዳይ እንዲመከርና በቂ መረጃ እንዲኖረው በመጥራት በጋራ እንደጥፋቱ ሁኔታ በሶስት ተከታታይ ጊዜ የቤተ ክፍሉ ሀላፊ ለተማሪው የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፣ የተማሪውን/ዋን ችግር ለይቶ የማወቅ ስራ ይሰራል፣ ወላጅ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ይደረጋል፣

         3.2.3. ተማሪው ከወላጁና ከቤተ ክፍሉ ኃላፊ የተሰጠውን የምክር አገልግሎት ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ካልቻለ፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ይደረጋል፣ ወላጆችም በአራተኛው የግንኙነት ጊዜ ይህንን እንዲያውቁ ይደረጋል፣

    አንቀፅ 4፡ የተማሪዎችን ባህሪ በተመለከተ መረጃ ስለማደራጀት

      4.1.የቤተ ክፍል ኃላፊው የተማሪዎቹን የዕለት ከዕለት የባህሪና ትምህርትን የመከታተል ሁኔታዎች በተመለከተ በቂ መረጃ ከክፍል አለቃዎችና ከመምህራን በመውሰድ ተማሪውን/ዋን ሊገልጻት/ጸው የሚችል መረጃ ይይዛል፡፡

      4.2.ተማሪው/ዋ በት/ቤት ውስጥ ከትምህርት ገበታው/ዋ ሊያስወጣት የሚችል ሁኔታ ሲፈጠር የቤተ ክፍሉ ኃላፊ ገላጭ የሆነ በየጊዜው የተመዘገበ መረጃ በግንኙነት መፅሀፍ አማካኝነት እና  ከወላጁ ጋር የተደረገ ውይይት፣ ተማሪው የፈረሙበትና ይቅርታ የጠየቁበት፣ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ አጠቃላይ የተማሪውን/ዋን ባህሪ ሊገልፅ የሚችል መረጃ ለት/ቤቱ ያቀርባል፣

      4.3.ከላይ የተመለከተውን መነሻ በማድረግ በጊዜው ከተፈፀመ የባህሪ ግድፈት ጋር በማየት የት/ቤቱ የዲስኘሊን ኮሚቴ በተማሪው/ዋ ላይ አግባብነት ያለው እርምጃ ይወስዳል፣

     

    አንቀጽ 5፡ ለአንድ አመት ከት/ቤት የሚያስወግዱ ጥፋቶች

            5.1. ት/ቤቱና ወላጅ ባላወቁት እና አሳማኝ ባላሆኑ ምክንያቶች ከት/ቤት በአመቱ የትምህርት ካላንደር 2ዐ% አለመገኘት፣

            5.2. በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ሲጋራ ማጨስ፣ ጫት መቃምና የተለያዩ አደንዛዥ ፅጾችን መጠቀም የአልኮል መጠጥ መጠጣትና ይዞ መገኘት፣

            5.3. በግልም ሆነ በቡድን አምባጓሮ መፍጠር ፣

            5.4. የት/ቤቱን ንብረት ሆን ብሎ መስበር፣ ማበላሸት ማጥፋት፣

            5.5. በፈተና ወቅት ማወክ፣ የፈተና ሰርዓቱ እንዲደናቀፍ ማድረግ፤መኮረጅና ማስኮረጅ፣

            5.6. የት/ቤቱን መምህራንና ሠራተኞች ኃላፊዎችን መሳደብና ማንጓጠጥ፣

                5.7. ተማሪዎችን መደብደብ ንብረት መንጠቅ ማስፈራራት፣

          5.8. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ በመጠቀም ተገቢ ያልሆነ ተግባር ማከናወን (ተማሪ የሚያወናብዱ መረጃዎች ማስተላለፍ፤ኩረጃ ወዘተ)

    አንቀፅ 6 ፡በማንኛውም ጥፋት በተደጋጋሚ የቤተ ክፍሉና ወላጅ ያደረጉትን ጥረት ተግባራዊ ባለማድረግ በአንቀፅ አስራ አንድ ላይ በንዑስ አንቀፅ 3.2.3 ላይ የተመለከተውን የማስጠንቀቂያ ጽሁፍ ተቀብሎ መስተካከል ያልቻሉ ተማሪ ለአንድ አመት ከት/ቤት ይታገዳል፣

    አንቀፅ 7፡ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከት/ቤት የሚያስወጡ ጥፋቶች

    7.1. በት/ቤት ውስጥና አካባቢ ማንኛውንም አደገኛ መሣሪያዎች ይዞ መገኘት፣

    7.2. ማንኛውንም የሰርቆት ተግባር ሲፈፅም የተገኘ ፣

    7.3. የት/ቤቱን ንብረትን ሆን ብሎ ለጉዳት ማጋለጥ፣

    7.4. በት/ቤት ውስጥና አካባቢ ሴት ወይም ወንድ ተማሪዎችን መድፈር ወይም ለመድፈር መሞከር፣

    7.5. ያልተፈቀዱ ስብሰባ፤በዓላት የማክበር ስነ-ስርዓት ማድረግ፣ ሁከት መፍጠር፤ ማሳደምና ከደንብ ልብስ ላይ ተገቢ ያልሆነ ፅሁፍ መፃፋና ቀጥሎ ማሰፋት

    7.6. በፈተና ወቅት ለሌላ ተማሪ መፈተን ወይም ለራስ ማስፈተን፣

    7.7. የተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ አቅርቦ መገኘት፣

    7.8. መምህራንና የትምህርት ቤቱን ሠራተኞች ለመደባደብ መሞከር መደባደብ፣

    7.9. የተማሪን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥልና እስከ ህይወት ማጥፋት የሚያደርስ ድርጊት

    7.10. ኢ ስነ-ምግባራዊ አለባበስ፤ልብስ መቅደድና ማቃጠል፤እራቁት ጭፈራ በትምህርት ቤት ጊቢ ውስጥ ማካሄድ

    • 11. ለመምህራን የእጅ ስልክ ብር ማሸጋገር (ትራንስፈር ማድረግ) ፣ የቤት ውስጥ አስጠኝ አድርጎ መቅጠር

    አንቀፅ 8፡- የደንብ ልብስ አጠቃቀም

    8.1. የተማሪዎች የደንል ልብስ የጨርቅ ዓይነት፤ጥራት እና ቀለም በትምህርት ቤቱ አስተዳደር፤ተማሪዎችና ወላጆች የጋራ ስብሰባ በውይይት የሚወሰን ይሆናል፡፡

    8.2. የወንድ ተማሪዎች የደንብ ልብስ አዘገጃጃት የሱሪ ቬሎ መጠን ከ18 ኢንች ያነሰ ሊሆን አይችልም፡፡ ሱሪ የሚለብሱ ሴት ተማሪዎችም በዚሁ መጠን የሚያዘጋጁ ይሆናል፡፡

    8.3. የሴት ተማሪዎች የደንብ ልብስ አዘገጃጃት የቀሚስ መጠን ከጉልበት በታች የታፋቸውን 2/3ኛ ክፍል የሚሸፍን መሆን ይኖርበታል፡፡

    8.4 ማንኛውም ተማሪ በጋራ ከተወሰነው የደንብ ልብስ ዓይነት፤ጥራትና ቀለም ውጪ መጠቀም አይፈቀድም፡፡

    8.5. ከት/ቤቱ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም ዓይነት ፅሁፍ ማሳተም፤ሌላ የጨርቅ ዓይነት ቀጥሎ ማሰፋት እና ያልተፈቀደ የደንብ ልብስ ዓይነት ፤ቅርፅና ይዘት መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

    8.6. በህግ በሀይማኖት ምክንያት ከተፈቀደ የደንብ ልብስ ውጪ ማንኛውንም ዓይነት አልባሳት ወደ ትምህርት ቤት ግቢ ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

    አንቀፅ 19፡- የተማሪዎች የፀጉር አቆራረጥ

    9.1.የተማሪ ፀጉር ንፅህና የተጠበቀ መሆን ይኖርበታል፡፡

    9.2.ለተማሪዎች ፀጉር ቀለም መቀባት አይፈቀድም፡፡

    9.3.የወንድ ተማሪ ፀጉር አቆራረጥ አጭርና ያልተበላለጠ መሆን ይኖርበታል፡፡

    9.4.ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸውን ማበጠርና ማስያዝ ይኖርባቸዎል፡፡

    9.5.ለሴት ተማሪዎች ተንጠልጣይ የጀሮ ጉትቻ/ጌጥ/ ማድረግ አይፈቀድም፡፡ ለወንድ ተማሪ ምንም ዓይነት የጀሮ ጉትቻ/ጌጥ/ ማድረግ አይፈወድም፡፡

    9.6.ለተማሪዎች በክፍል ውስጥ መጥፎ ሽታ ያለው ቅባት ተቀብቶ መምጣት አይፈቀድም፡፡

     

    አንቀፅ 9፡- ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

    9.1.በተለያዩ ከዲስኘሊን ግድፈት ውጭ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ያቋረጡበትን ተገቢ መረጃ እያቀረቡ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋል፣

    9.2.ከአንድ ት/ቤት በዲስኘሊን ግድፈት የተቀጣ ተማሪ ትምህርት ቤቱን ለቆ ሲሄድ ወይም መልቀቂያ ሲጠይቅ ስለተማሪው ሁኔታ በግልፅ በትራንስክሪኘቱ ላይ ይገለፃል፡፡

    9.3.የታገደ ተማሪ እገዳውን እስከ ሚጨርስ የትምህርት ማስረጃው አይሰጠውም፡፡

    9.4. በመመሪያው ውስጥ የተጠቀሱ የዲስኘሊን ጥፋቶች የዲስኘሊን ኮሚቴ ከሚወስነው ውሳኔ በተጨማሪ እንደየጥፋቱ ሁኔታ ፍርድ ቤት ሊያስጠይቅ ይችላል፡፡

    9.5.ለተማሪዎች በሚሰጠው ተከታታይ ትምህርትና ምከር አገልግሎት፣ የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ሠራተኞች፣ የተማሪዎች መማክርት፣ መምህራን፣ የሥነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መምህራን፣ ወላጅ፣ ተማሪ፣ መምህር ህብረት የሚኒ-ሚዲያ አገልግሎት ሁሉ በቅንጅት ለተማሪዎች ባህሪ መሻሻል ይሰራሉ፡፡

    አንቀፅ 10 ፡- በሰዓቱ የትምህርት አገልግሎት  ክፍያ ለማይፈፅሙ

    ክፍያው  ከሚፈፀምበት  ቀናት   በኃላ  ክፍያ የሚፈፅሙ ወላጆች   ቅጣት ውስጥ ይገባሉ፡፡ 

    ክፍያውን እንዲያጠናቅቁ እስከ 30 ቀን ከታገሰ በኋላ ተማሪው በትምህርት ገበታው ላይ እንዳይገኝ ያደርጋል፡፡

    መሰከረም 2016 ዓ.ም

    አዲስ አበባ

Admissions

Visits and Enquiries

The School Admissions Procedure ensures a fair and straightforward admissions system that promotes equity and fair access for all.

Applications for admission are accepted throughout the school year and families are encouraged to make an appointment for an interview and tour of the school. For the admission file to be complete we require the following:

  1. Completed and Signed Registration File

  2. Completed and Signed Medical Form

  3. Two passport size photographs

  4. Copies of the Parents’ ID card

    Please be aware that places can only be guaranteed by signing an School Contract and paying all tuition and fees by the due date noted on the invoice

Ardi Youth Academy

Ardi Youth Academy aims at providing an outstanding education for students. We strongly believe that knowledge without discipline is ignorance. Hence we focus on students’ behavioral and educational maturity at the same time.

Get in Touch!

Address

Addis Ababa, Addis Ketema
Sub city Wereda-13 around Birchiko Factory

Email

ardiyouthacademy@gmail.com

Phone

+2519 42151515

Scroll to Top